ደራሲ፥ Soccer Ethiopia ሶከር ኢትዮጵያ

ሶከር ኢትዮጵያ በኢትዮጵያ እግር ኳስ ላይ ብቻ ትኩረቱን አድርጎ የሚሰራ የኦንላይን ሚድያ ነው።

የትግራይ ክለቦችን መልሶ ለማቋቋም የታሰበው የቴሌቶን መርሐግብር ዛሬ ይከናወናል

“ክለቦቻችንን እንታደግ” በሚል መሪ ቃል ከውድድር ርቀው የነበሩትን የትግራይ ክለቦች መልሶ ለማቋቋም ዛሬ ምሽት በሸራተን አዲስ ሆቴል ታላቅ የቴሌቶን መርሐግብር ይደረጋል። በ2013 የመጀመሪያ ወራት በትግራይ ክልል በተቀሰቀሰው ጦርነት ምክንያት ከውድድር……

ሪፖርት | የመቻሎች ድል የሊጉን የዋንጫ ፉክክር ከሳምንት ሳምንት አጓጊ አድርጎታል

ምሽት ላይ የተካሄደው እና የዋንጫ ፉክክሩን የሚወስነው ጨዋታ መቻልን ባለ ድል አድርጎ መቻል የመሪውን ኮቴ እግር በእግር መከተሉን አጠናክሮ ቀጥሎበታል። ባለሜዳዎቹ ሲዳማ ቡናዎች ከድል መልስ ቡልቻ ሹራ፣ በዛብህ መለዮ፣ ሀብታሙ……

“ስለ አቡበከር ናስር ማውራት አልፈልግም”

ኢትዮጵያዊው ከብራዚላውያኑ ጋር ያለው እህል ውሃ ያበቃ ይመስላል….. ከወራት በፊት በሰጡት መግለጫ ላይ ኢትዮጵያዊው አቡበከር ናስር ለእግር ኳስ ሕይወቱ አደጋ የሆነ ጉዳት እንዳጋጠመው፤ ለማገገም በጣም እየታገለ እንዳለ እና በቅርቡ ይመለሳል……

ሪፖርት | ቡናማዎቹ የኢትዮጵያ መድንን የተከታታይ የሰባት ጨዋታ የድል ጉዞን ገተውታል

በዕለቱ ቀዳሚ ጨዋታ ኢትዮጵያ ቡና ተከታታይ አምስተኛ ድሉን በማሳካት ደረጃውን ሲያሻሽል ኢትዮጵያ መድኖች ከሰባት ተከታታይ የድል ጉዞ በኋላ ሽንፈት አስተናግደዋል። በዕለቱ ቀዳሚ ጨዋታ ኢትዮጵያ መድኖች ሻሸመኔ ከተማን 2ለ0 ካሸነፉበት አሰላለፍ……

መረጃዎች | 111ኛ የጨዋታ ቀን

28ኛ ሳምንት የሊጉ መርሐግብር ነገ ሲጀምር ላለመውረድ በሚደረገው ፉክክር ወሳኝ ሚና ያላቸውን ሁለት ጨዋታዎች ያስተናግዳል ፤ ጨዋታዎቹን የተመለከቱ መረጃዎች በተከታዩ ፅሁፍ ቀርበዋል። ሻሸመኔ ከተማ ከ ፋሲል ከነማ የጨዋታ ሳምንቱ የመክፈቻ…

ሪፖርት | ወላይታ ድቻዎች ከናፈቃቸው ድል ጋር ታርቀዋል

የዕለቱ ቀዳሚ መርሐግብር በነበረው ጨዋታ ወላይታ ድቻዎች ከመመራት ተነስተው ሀዲያ ሆሳዕናን 2-1 በመርታት ከአራት ጨዋታዎች በኋላ ወደ አሸናፊነት ተመልሰዋል። ወላይታ ድቻዎች በ26ኛ ሳምንት ከተጠቀሙት የመጀመሪያ 11 ምርጫቸው ሦስት ለውጦችን ሲያደርጉ…

ሪፖርት | ኢትዮጵያ መድን 7ኛ ተከታታይ ድሉን አሳክቷል

በ27ኛ ሳምንት የማሳረጊያ መርሐግብር ኢትዮጵያ መድን በሁለቱ አጋማሾች የመጨረሻ ደቂቃዎች ላይ በተገኙ ግቦች ሰባተኛ ተከታታይ ድላቸውን ሻሸመኔ ከተማ ላይ አስመዝግበዋል። ኢትዮጵያ መድኖች አዳማ ከተማን ከረቱበት የመጀመሪያ 11 ምርጫ ባደረጉት ብቸኛ…

በሴካፋ ካጋሜ ካፕ ኢትዮጵያ እንደማትወከል ታወቀ

በ13 ክለቦች መካከል እንደሚደረግ የሚጠበቀው የሴካፋ ካጋሜ ካፕ ውድድር ላይ የሚሳተፉ ክለቦች ሲለዩ የውድድሩ ቀንም ማሻሻያ ተደርጎበታል። የምስራቅ እና መካከለኛውን የአፍሪካ ሀገራትን ያቀፈው ሴካፋ የቀጠናውን የተለያዩ የብሔራዊ ቡድኖች ውድድር ከማዘጋጀቱ…

ለቡድኑ ዝቅተኛ ግምት ባለመስጠት ጨዋታውን አሸንፈን መውጣት እንዳለብን ነው የተነጋገርነው

የኢትዮጵያ ብሄራዊ ቡድን ዋና አሰልጣኝ ገብረመድህን ኃይሌ ከዛሬው ጨዋታ በፊት ከኢትዮጵያ እግር ኳስ ፌደሬሽን የሚድያ ክፍል ጋር ቆይታ አድርገዋል። የብሄራዊ ቡድኑ አባላት በጥሩ ሁኔታ ላይ እንዳሉ በመግለፅ የዛሬውን ጨዋታ ለማሸነፍ…

‘የዱር ውሾቹን’ የተመለከቱ አንዳንድ መረጃዎች

በነገው ዕለት የኢትዮጵያ ብሄራዊ ቡድንን በሜዳዋ የምትገጥመውን ጊኒ ቢሳው የተመለከቱ መረጃዎች እንደሚከተለው አጠናክረናል። የኢትዮጵያ ብሄራዊ ቡድን ለ2026 የዓለም ዋንጫ ለማለፍ እየተካሄደ ባለው የማጣርያ ውድድር ሦስተኛ ጨዋታውን ለማከናወን ጊኒ ቢሳው ደርሷል…