አርባ ስምንት ከሚሆኑ የአፍሪካ ሃገራት መሪዎች ጋራ ጉባኤ ተቀምጣ የነበረችው ደቡብ ኮሪያ፣ በማዕድን፣ ኃይል እና የፋብሪካ ምርቶችን የተመለከቱ 47 ስምምነቶችን ተፈራርማለች፡፡

ደቡብ ኮሪያ ከአፍሪካ ጋራ ለመጀመሪያ ጊዜ ባካሄደችው ምክክር፣ ከ23 ሃገራት ጋራ ስምምነት ስትፈራረም፣ አህጉሪቱ ያላትን ሰፊ የማዕድን ሃብት እና የውጪ ንግድ ለመጠቀም በማለም እንደሆነ ተመልክቷል።

በዓለም ያለው የአቅርቦት ሰንሰለት በጂኦፖለቲካ ችግሮች ምክንያት እየተስተጓጎለ በመሆኑ፣ የአፍሪካ ሚና አስፈላጊ ሆኖ መገኘቱን የደቡብ ኮሪያው ፕሬዝደንት ዩን ሱክ ዬዎል በጉባኤው ላይ ተናግረዋል።

በማዕድን ረገድ ከአፍሪካ ሃገራት ጋራ ሽርክና መፍጠር እንደሚሹም ፕሬዝደንቱ ጨምረው ተናግረዋል።

ደቡብ ኮሪያ ለአፍሪካ የምታደርገውን የልማት ድጋፍ ወደ 10 ቢሊዮን ዶላር ማሳደግ እንደምትሻና የውጪ ንግድን ለመደገፍና የደቡብ ኮሪያ ኩባንያዎች በአፍሪካ መዋዕለ ነዋይ እንዲያውሉም 14 ቢሊዮን ዶላር እንደመደበች ፕሬዝደንቱ አስታውቀዋል።

By VOA News Amharic

VOA አማረኛ, provides various news and information in Amharic

ምላሽ ይስጡ

ኢ-ፖስታ አድራሻወ ይፋ አይደረግም። መሞላት ያለባቸው መስኮች * ምልክት አላቸው