ረቡዕ ግንቦት 21 ቀን 2016 (አዲስ ማለዳ) የኢትዮጵያ ሀገራዊ ምክክር ኮሚሽን የምክክር ምዕራፍ ማስጀመሪያ መድረክ ላይ ዋና ኮሚሽነር ፕሮፌሰር መስፍን አርዓያ የአገራዊ ምክርር ኮሚሽን ሂደት መጀመሩን ተከትሎ “አዲስ ውጤት ለማግኘት በአዲስ መንገድ መሄድ አስፈላጊ ነው” ሲሉ ገልጸዋል።

በመድረኩም የኢትዮጵያ ሀገራዊ ምክክር ኮሚሽን ሕዝቡ በተወካዮቹ አማካኝነት ትርጉም ያለው ተሳትፎ በማድረግ፤ ስር የሰደዱ ችግሮችን ምንጭ ከመለየት ጀምሮ በምክክር ሂደቱ ከሌሎች ባለድርሻ አካላት እኩል የሚሳተሳተፉበት መድረክ ነው።

ይህ የምክክር ሂደት “በመንግሥት እና በሕዝብ መካከል ያለውን ግንኙነት ለማሻሻል፣ መተማመን የሰፈነበት አዲስ የፖለቲካ ሥርዓት ለመፍጠር፤ ለዘመናት ሲንከባለሉ የመጡ ውስጣዊ ችግሮቻችንን በውይይት ለመፍታት የሚያስችል የፖለቲካ ባህል ለማዳበር ብሎም ወደ እልቂት የማንገባበትን ሁኔታ ለመፍጠር ያስችላል” ሲሉ ፕሮፌሰር መስፍን ተናግረዋል።

እንዲሁም ወቅታዊ ችግሮችን ዘላቂ በሆነ መንገድ በመፍታት ሰላምን አስተማማኝ በሆነ መሠረት ለማቆም እንዲሁም ጠንካራና ቅቡልነት ያለው ሀገረ መንግሥት ለመገንባት የሚደረገው ጥረት በስኬት እንዲቋጭ ምክክሩ ወሳኝ መሆኑም ተመላክቷል።

የኢትዮጵያ ሀገራዊ ምክክር ኮሚሽን የከተማ አስተዳደርና ክልላዊ የምክክር ምዕራፍ ዛሬ በአዲስ አበባ ከተማ ተጀምሯል።

By Addis Maleda

አዲስ ማለዳ ወቅታዊ የአገራችንን ጉዳዮች በስፋትና በጥልቀት የምትተነትን፣ የብዙኃን መገናኛ ናት።