ፈቃዳቸው የተሠረዘው የትምህርት ፖሊሲውን ባለመጠበቅና መስፈርቱን ባለማሟላታቸው ነው ብሏል ባለስልጣኑ፡፡ ባለስልጣኑ በ2017 ዓ.ም የትምህርት ዘመን ተማሪዎችን መዝግበው የሚያስተምሩ ትምህርት ቤቶችን እና ፈቃዳቸው የተሠረዘ የትምህርት ተቋማትን ይፋ አድርጓል፡፡

በዚህም በ2017 ዓ.ም የትምህርት ዘመን ተማሪዎችን መዝግበው የሚያስተምሩ ትምህርት ቤቶች 1 ሺህ 332 ሲሆኑ÷ የማስተማር ፈቃድ እንደተሰጣቸውም ገልጿል፡፡

በሌላ በኩል 43 ትምህርት ቤቶች በራሳቸው ጊዜ መቀጠል ስላልቻሉ ፈቃዳቸው ተሠርዟል መባሉን የባለስልጣኑ መረጃ አመላክቷል፡፡

እንዲሁም 150 ትምህርት ቤቶች ጉዳያቸው በሂደት ላይ መሆኑና ወደፊት እንደሚገለጽ ተጠቁሟል፡፡

41 ትምህርት ቤቶች ደግሞ የትምህርት ፖሊሲውን ባለመጠበቅና መስፈርቱን ባለማሟላታቸው ፈቃዳቸው መሠረዙን ነው ባለስልጣኑ ያስታወቀው፡

ሰኔ 10 ቀን 2016 ዓ.ም

By Ethio FM 107.8

Ethio FM is news website and popular radio station in Ethiopia.

ምላሽ ይስጡ

ኢ-ፖስታ አድራሻወ ይፋ አይደረግም። መሞላት ያለባቸው መስኮች * ምልክት አላቸው