አምራቾች ወደ ምርት ከመግባታቸው በፊት ደረጃዎችን  ገዝተው በዛ ደረጃ መሰረት ወደ ምርት ዝግጅት እና ወደ ማምረት ስራ ውስጥ እንደሚገቡ በኢትዮጲያ ደረጃዎች ኢንስቲትዩት የህዝብ ግንኙነት እና ኮምንኬሽን ስራ አስኪያጅ  አቶ ብሩክ ሀብቴ ለኢትዮ ኤፍ ኤም ተናግረዋል

የደረጃ ግዢውንም ከዚ ቀደም በአካል በመገኘት እንደሚፈፅሙ እና አሁን ላይ ግን ባሉበት ሆነው መግዛት የሚችሉበት ዘመናዊ አሰራር እንደተዘጋጀ ገልፀዋል።

ተቋሙ በዋናነት ትኩረት አድርጎ ከሚሰራቸው ስራዎች ውስጥ የኢትዮጵያ ደረጃዎችን ማዘጋጀት  ፣ በተዘጋጁ ደረጃዎች ላይ የቴክኒክ ድጋፍ ማድረግ እና ስልጠና መስጠት እንዲሁም ጥናት እና ምርምር ስራዎችን መስራት ይጠቀስበታል ብለዋል ።

ደረጃዎች የሚዘጋጁትም ሀገር ውስጥ ባሉ የተለያዮ ባለሙያዎች እንደሆነ አስታውቀዋል።

ደረጃ የሚዘጋጅባቸው 7 ዘርፎች እንዳሉ የነገሩን ስራ አስኪያጁ በነዚህም 7 ዘርፍ ውስጥ 112
የቴክኒክ አባላት እንዳሉት አንስተዋል።

የቴክኒክ  ኮሚቴ አባል የሆኑም 402 ተቋማት መኖራቸውን እና እነዚህም የምርምር ተቋማትን፣ ዮኒቨርስቲዎችን እና አምራች ድርጅቶችን ያካተተ መሆኑን ተናግረዋል።

ሐመረ ፍሬው
ሰኔ 10 ቀን 2016 ዓ.ም

By Ethio FM 107.8

Ethio FM is news website and popular radio station in Ethiopia.

ምላሽ ይስጡ

ኢ-ፖስታ አድራሻወ ይፋ አይደረግም። መሞላት ያለባቸው መስኮች * ምልክት አላቸው