ካውሰር PLC( ሻሊና ሄልዝ ኬር) በአለም አቀፍ ደረጃ ትልቅ ተቀባይነትን ያተረፈ ድርጅት ሲሆን በኢትዮጵያ ይዟቸው የመጣቸውን አዳዲስ ምርቶች ሰኔ 6/2016 ዓ.ም አስተዋውቋል።

ከነዚህ ምርቶች ውስጥ አንዱ ሞናሊሳ ሲባል ይህም የቆዳ እንክብካቤን ለመጠበቅ የሚያስችል ሎሽንና ክሬም ነው

ኤፒግሎው የተሰኘው ደግሞ ለአፍሪካ ቆዳ የተዘጋጀ ሲሆን እንደ ጥቁር ነጠብጣቦች እና ዥንጉርጉር ፊትን እና የተለመዱ የቆዳ ስጋቶችን በ28 ቀናት ውስጥ በመቀነስ ብቻ የሚታይ ለውጥ የሚሰጥ የቆዳ መንከባከቢያ እንደሆነ ተገልጿል

ሌላው ፍሎደንት የተባለው የጥርስ ሳሙና ምርት ሲሆን በፍሎራይድ ለተጠቃ ጥርስ፣ ለአፍ ጤንነት፣ የጥርስ መቦርቦርን የሚታደግ እንደሆነ ተነግሯል።

የመጨረሻው ምርት ጀርሞል የተሰኘ ሳሙና ሲሆን  ሰውነትን ከጀርሞች ለመከላከል የሚረዳ ነው ተብሏል።

ሻሊና ሄልዝ ኬር 40 አመትን ያስቆጠረ ድርጅት ሲሆን እስካሁን በ22  የአፍሪካ ሀገራት ላይ ሰርቷል።

ድርጅቱ በአሁን ሰአት በአዲስ አበባ ላይ 6 ክፍለ ከተሞች ላይ ስራ የጀመረ ሲሆን 1000 ለሚደርሱ ሰዎች የስራ እድል ፈጥሯል።

By Ethio FM 107.8

Ethio FM is news website and popular radio station in Ethiopia.

ምላሽ ይስጡ

ኢ-ፖስታ አድራሻወ ይፋ አይደረግም። መሞላት ያለባቸው መስኮች * ምልክት አላቸው