ዓርብ ሰኔ 07 ቀን 2016 (አዲስ ማለዳ) በአፋር እና ሶማሊ ክልል አዋሳኝ አካባቢዎች የተኩስ አቁም ስምምነቱ ተጥሶ የተጀመረው የትጥቅ ውጊያ እንዲሁም የንጹሀን ጉዳትና መፈናቀል እንዳሳሰበው የኢትዮጵያ ሰብዓዊ መብቶች ኮሚሽን አስታወቀ።

ከባለፈው ሳምንት ሐሙስ ግንቦት 30 ቀን 2016 ጀምሮ በአካባቢው ወደ ትጥቅ ውጊያ ያመራ ውጥረት መከሰቱን በተመለከተ መረጃዎች እንደደረሱት ኢሰመኮ ገልጿል።

ኮሚሽኑ ከአፋር እና ሶማሊ ክልል አመራሮች እንዳረጋገጠው በአዋሳኝ አካባቢው “አልፎ አልፎ” ውጊያ ተከስቷል። በውጊያውም ቁጥራቸው በመግለጫው ያልተጠቀሱ ንጹሀን ሰዎች መጎዳታቸው እና መፈናቀላቸው ተጠቁሟል።

የኢሰመኮ ምክትል ኮሚሽነር ራኬብ መሰለ ግጭቱ በአስቸኳይ እንዲቆም የሁለቱ ክልል አስተዳደሮች ዝግጁ በመሆናቸው የፌደራል መንግስቱ ተጨማሪ ድጋፍ እንዲያደርግ ጠይቀዋል። በተጨማሪም ተፋላሚዎች በኢድ አል አድሃ በዓል መንፈስ ተግባብተው ውጊያው እንዳይባባስ እና ንጹሀን እንዳይጎዱ እንዲያደርጉ ጥሪ አቅርበዋል።

በድንበርተኞቹ የአፋር ሕዝቦች እና ኢሳ በሚል መጠሪያ በሚታወቁት በሶማሌ ክልል የሚኖሩ ጎሳዎች መካከል የሚነሱ ግጭቶች ሚያዝያ 10 ቀን 2016 የኢትዮጵያ እስልምና ጉዳዮች ጠቅላይ ምክር ቤት ባዋቀረው 25 አባላት ያሉት የእርቀ ሰላም ኮሚቴ አማካኝነት የተኩስ አቁም ስምምነት ለማድረግ ተስማምተው እንደነበረ አዲስ ማለዳ መዘገቧ አይዘነጋም።

By Addis Maleda

አዲስ ማለዳ ወቅታዊ የአገራችንን ጉዳዮች በስፋትና በጥልቀት የምትተነትን፣ የብዙኃን መገናኛ ናት።

One thought on “በአፋርና ሶማሊ ክልል አዋሳኝ ቦታዎች ያለው ውጊያ አሳሳቢ ነው- ኢሰመኮ ”
  1. 24/7.
    Профессиональный сервис сантехников в Сан-Хосе.
    Надежные сантехники в Сан-Хосе.
    без выходных.
    Специальные цены на услуги сантехников в Сан-Хосе.
    Экспертные сантехнические услуги в Сан-Хосе.
    24 часа в сутки.
    Экспертные сантехнические услуги в Сан-Хосе.
    Надежные сантехники в вашем районе.
    Доступные цены на сантехнические услуги в Сан-Хосе.
    plumber in san jose plumbersan-joseca4.com .

ምላሽ ይስጡ

ኢ-ፖስታ አድራሻወ ይፋ አይደረግም። መሞላት ያለባቸው መስኮች * ምልክት አላቸው