በምስራቅ ህንድ ዌስት ቤንጋል በሁለት ባቡሮች ግጭት ነው አደጋው የደረሰው ። ፖሊስ በህይወት የተረፉ ሰዎችን ለመታደግ ጥረት እየተደረገ መሆኑንና የአደጋውን መንስኤ እያጣራ መሆኑን አስታውቋል።

በህንድ በደረሰ የባቡር ግጭት አደጋ እስካሁን የ13 ሰዎች ህይወት ሲያልፍ 30 ሰዎች ደግሞ ጉዳት እንደደረሰባቸው ተነግሯል።

አደጋው የደረሰው የመንገደኞች እና እቃ ጫኝ ባቡሮች በመጋጨታቸው እንደሆነ የገለጸው የአካባቢው ፖሊስ የአደጋውን መንስኤ እያጣራሁ ነው ብሏል።

በምስራቅ ህንድ ዌስት ቤንጋል ክልል የደረሰውን አደጋ ተከትሎ የነፍስ አድን ሰራተኞች በሕይወት የተረፉ ሰዎችን በማፈላለግ ላይ ይገኛሉ።

የአደጋው መንስኤ ምን እንደሆነ ያልገለጸው ፖሊስ በአሁኑ ወቅት ሰዎችን ለማትረፍ ርብርብ በመደረግ ላይ ነው ብሏል።

የሀገሪቱ የባቡር ትራንስፖርት ሚንስትር አሽዋኒ ቫይሽናው የመንገደኞች ባቡሩ በእቃ ጫኝ አውሮፕላን ከኋላው በመገጨቱ አደጋው መድረሱን ገልጸው ዝርዝር ጉዳዮች ከሙሉ ምርመራው በኋላ ይፋ ይደረጋል ነው ያሉት።

በአደጋው እስካሁን የ13 ሰዎች ህይወት ያለፈ ሲሆን ቁጥሩ ከዚህም ሊጨምር እንደሚችል ቢቢሲ ዘግቧል።

የ1.4 ቢሊየን ህዝብ ባለቤት በሆነችው ህንድ በከተማ ውስጥ እና ከከተማ ውጭ ለሚደረግ ጉዞ ባቡር ቀዳሚው የትራንስፖርት አማራጭ ነው።

ባለፉት አመታትም በርካታ አሰቃቂ የባቡር አደጋዎች ተከስተው የብዙ ሰዎችን ህይወት ነጥቀዋል።

ለአብነት በባለፈው አመት በሀገሪቱ ምስራቅ ክፍል ሶስት ባቡሮች ተጋጭተው 290 ሰዎች ሲሞቱ ከአንድ ሺህ የሚልቁት ደግሞ መጎዳታቸው ይታወሳል።

By Al Ain Amharic News

አል ዐይን ኒውስ ሁሉን አቀፍ ሽፋን የሚሰጥ እና የዓለም ክስተቶችን በወቅቱና በጊዜው ለተከታዮቹ ያቀርባል፡፡

ምላሽ ይስጡ

ኢ-ፖስታ አድራሻወ ይፋ አይደረግም። መሞላት ያለባቸው መስኮች * ምልክት አላቸው