ኪም የበላይነት እና ኢምፔሪያሊዝምን ለማስቀጠል የሚጥረውን የምዕራባውያን ፓሊሲ እንዋጋለን የሚለውን የፑቲን መግለጫ እስተጋብተዋል። ዋሽንግተን እና ሴኡል እየጠነከረ የመጣው የሩሲያ እና ሰሜን ኮሪያ ግንኙነት ስጋት ውስጥ እንዲገቡ አድርጓቸዋል።

ሰሜሪ ኮሪያ እና ሩሲያ ከሁለቱ በአንደኛቸው ላይ ወታራዊ ጥቃት በሚቃጣበት ወቅት ወታራዊ ድጋፍ ለማቅረብ የሀገራቱ መሪዎች ስምምነት ላይ ደርሰዋል።

ይህ ስምምነት የተደረሰው የሩሲያው ፕሬዝደንት ቭላድሚር ፑቲን ከ24 አመታት በኋላ ለመጀመሪያ ጊዜ በሰሜን ኮሪያ ጉብኝት ባደረጉበት ወቅት ነው።

ስምምነቱ ሁለቱ የቀዝቃዛው ጦርነት አጋሮች በፈረንጆች 1961 ተፈራርመውት የነበረው እና ሶቬት ህብረት ከደቡብ ኮሪያ ጋር ዲፕሎማሲያዊ ግንኙት ስትጀምር ተሰርዞ የነበረውን ወታደራዊ ትብብር የሚያድስ ነው ተብሏል።

“ኮምፕሬሄንሲቭ ስትራቴጂክ ፓርትነርሺፕ” ለማድረግ በሩሲያው ፕሬዝደንት ፑቲን እና በሰሜን ኮሪያው መሪ ኪም ጆንግ ኡን መካከል በትናንትናው እለት የተደረሰው ስምምነት ሞስኮ በአመታት ውስጥ በእስያ አህጉር ያደረገችው ትልቅ እርምጃ ነው።

“ከሁለቱ በአንደኛቸው ላይ ጦርነት የሚታወጅ ከሆነ ወይም በጦርነት ውስጥ ካለ፣ በተመድ ቻርተር አንቀጽ 54 መሰረት ሌላኛው ሁሉንም አይነት ወታራዊ እና ሌሎች ድጋፎችን ወዲያውኑ ያቀርባል” ይላል የስምምነቱ አንቀጽ አራት።

የተመድ ቻርተር አንቀጽ 51 አባል ሀገራት ወረራ ሲፈጸምታቸው በተናጠል ወይም በቡድን ራሳቸውን መከላከል እንደሚችሉ ያስቀምጣል።

ስምምነቱ ሩሲያ በዚህ ምዕተ አመት የኑክሌር ጦር መሳሪያ የሞከረችውን ሰሜን ኮሪያን ምን ያህል ልትረዳት ትችላለች የሚል ምዕራባውያንን ስጋት ውስጥ ከቷቸዋል።

ኪም የበላይነት እና ኢምፔሪያሊዝምን ለማስቀጠል የሚጥረውን የምዕራባውያን ፓሊሲ እንዋጋለን የሚለውን የፑቲን መግለጫ እስተጋብተዋል።

ሁለቱ ሀገራት እንዳቸው የሌላኛቸውን ጥቅም የሚጻረር ስምምነት ከሶስተኛ ሀገር ጋር እንዳይፈራረሙ እና ግዛታቸውንም ደህንነት እና ሉአላዊነት ለሚጎዳ ሌላ ሀገር ላለማስጠቀምም ተስማምተዋል ተብሏል።

በተጨማሪም የቀጣናውን ብሎም አለምአቀፍ ሰላምን ለማስፈን ወታራዊ አቅማቸውን ለማጠናከር የሚያስችሉ እርምጃዎችን ይወስዳሉ።

ፕሬዝደንት ፑቲን፣ ሩሲያ በዩክሬን ለምታካሂደው ወታደራዊ ዘመቻ ሙሉ ድጋፍ የሰጠችውን ሰሜን ኮሪያን አመስግነዋል።

ጃፓን ሩሲያ ከሰሜን ኮሪያ ጋር ያላት ትብብር እንደሚያሰጋት ገልጻለች። 

ከሰሜን ኮሪያ ፖለቲካዊ እና ኢኮኖሚ ዋና ተጠቃሚ የሆነችው ቻይና በሁለቱ ሀገራት ግንኙነት ጉዳይ ምንም ማለት አልፈለገችም።

ዋሽንግተን እና ሴኡል ግን እየጠነከረ የመጣው የሩሲያ እና ሰሜን ኮሪያ ግንኙነት ስጋት ውስጥ እንዲገቡ አድርጓቸዋል።

ምዕራባውያን ሰሜን ኮሪያ ሩሲያ በዩክሬን ለምታደርገው ጦርነት ጥቅም ላይ የሚውል የጦር መሳሪያ ታቀርባለች ሲሉ ይከሷታል። ሰሜን ኮሪያ ግን የሀሰት ፕሮፓጋንዳ ነው አስተባብላለች።

By Al Ain Amharic News

አል ዐይን ኒውስ ሁሉን አቀፍ ሽፋን የሚሰጥ እና የዓለም ክስተቶችን በወቅቱና በጊዜው ለተከታዮቹ ያቀርባል፡፡

ምላሽ ይስጡ

ኢ-ፖስታ አድራሻወ ይፋ አይደረግም። መሞላት ያለባቸው መስኮች * ምልክት አላቸው