ሰኔ 15 ቀን 2016 (አዲስ ማለዳ) በኢትዮጵያ የመጀመሪያው ነው የተባለው የሸገር ታላቁ የመንገድ ግንባታ ፕሮጀክት ማስጀመሪያ መርሐ-ግብር በኩራ ጂዳ ክፍለ ከተማ ተካሄደ።

በአምስት ዓመታት እንደሚጠናቀቅ የተመላከተው150 ኪሎ ሜትር የሚረዝመው መንገድ÷ ሁሉንም የሸገር ከተማ ክፍለ ከተሞች እንደሚያገናኝ ተገልጿል፡፡

በመጀመሪያው ዙር በ4 ነጥን 5 ቢሊየን ብር የ38 ነጥብ 5 ኪሎሜትር ግንባታ እንደሚከናወን የተገለጸ ሲሆን÷ ይህም ከኩራ ጅዳ በመነሳት ጣፎ፣ ኮዬ ፈጨ እና ገላን ክፍለ ከተሞችን ያገናኛል ተብሏል፡፡

በማስጀመሪያ መርሐ-ግብሩ ላይ የኦሮሚያ ክልል ርዕሰ መሥተዳድር ሽመልስ አብዲሳ፣ የኦሮሚያ መንገዶችና ሎጂስቲክ ቢሮ ኃላፊ ሄለን ታምሩ (ኢ/ር)፣ የሸገር ከተማ ከንቲባ ተሾመ አዱኛ (ዶ/ር) ተገኝተዋል።

By Addis Maleda

አዲስ ማለዳ ወቅታዊ የአገራችንን ጉዳዮች በስፋትና በጥልቀት የምትተነትን፣ የብዙኃን መገናኛ ናት።